Yared Zemenfes
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን! እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣው የተፈጠረበትን ሥርዓት ጠብቆ ነው፡፡ የዓለም ተፈጥሮም ያለ ሥርዓት ትርጉም የለውም፡፡ እናም በዚች ዓለም አግዚአብሔር አምላክ በአባቴና በእናቴ ላይ ምክንያት አድርጎ ፈጥሮኛል። ከተፈጠርኩም ጀምሮ ይኧው በአምላክ ቸርነት እስከ አሁን በህይወት አለሁ።
እንዲህ ሰው እንደ መሆኔ የራሴ ባህሪያት አሉኝ እነዚህም ያለመጨነቅ፡ከሰው ጋር ሁሉ መሳቅ፡ከሀዘን ይልቅ ደስታን የማበዛ፡ ለተፈጥሮአዊ ድንገተኛ ክስተቶች ብዙም የማልጨነቅ፡ ሰውን እንደ ሰውነቱ እንጂ እንደዘሩ ወይም እንደ ሀይማኖቱ የማልመለከት ሰው ነኝ።
መከራዬን በደስታ የለወጥክ አምላክ የችግሬ መፍትሄ የፈተናዬ መልስ የድካሜ ውጤት የጭንቀቴ ደራሽ እግዚአብሄር ተመስገንልኝ!!!
አንተ የምታውቀው ትናንትና ስላለፈው ነገር ብቻ ነው።እግዚአብሄር ግን የሚመጣውን ሁሉ ያውቃል። ሰው በትናንትና ጥፋት ይከሳል እርሱ ግን እንደ አባት ዛሬን በፍቅር ይቀበልሀል።